✍️ወደ አሩሲም ነይ ስደትሽ ካልቀረ የአምላክ እናቱ አሩሲም ዝለቂ በግፍ ለሚሞቱ ከትናንቱ በላይ ዛሬ ዘንበል በይ ግፉ በዝቷልና አሩሲም ቸል አትበይ በአንዱ ልጅሽ ላይ የታወጀው ሞቱ ዛሬም አማኞች ላይ ጸና መገፋቱ ድንግል ሆይ አትዘግዪ ዛሬም ደግመሽ ነይ ሕማም ላይ ነንና ከእኛ አትለዪ አሩሲንም ዝለቂ በግፍ ለሚሞቱ በልጅሽ ያመነ ተቀላ አንገቱ አዎ አትዘግዪ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሽ አንቺ ስትቀርቢን ጠላትም እንዲሸሽ (ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ)