የብራዚል የ2026/27 የቡና ገበያ አዝማሚያ ምን ይሆን? (የተፎካካሪን ሁኔታን መረዳት ምናልባትም ቀጣይ አቅጣጫ ለመንደፍ ያግዝ ይሆናል) ሳህለማርያም ገ/መድህን የብራዚል የ2026/27 የምርት ዘመን ትንበያ እንደሚያሳየው ሀገሪቱ ከ60 እስከ 75 ሚሊዮን ጆንያ የሚደርስ እጅግ ግዙፍ የቡና ምርት ለመሰብሰብ እየተዘጋጀች ይገኛል። ይህ ለዓለም አቀፉ ገበያ ትልቅ የምርት ማገገም ዜና ቢሆንም፣ በምርት ብዛትና በገበያ እውነታ መካከል ከፍተኛ…