ኤርትራ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ባድመ ማስጠጋቷ ተሰማ የኤርትራ መንግሥት በባድመ ከተማ አካባቢ ከሚገኘው ሰንበል እስከ ጓል ገምሃሎ ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ወታደሮችን ማሰማራቱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል (ኤ.ኤፍ.ፒ) ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ኤርትራ ወደ ባድመ አካባቢ ተጨማሪ ሠራዊትና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሊሻዎችን አስጠግታለች፤ ይህም በኢትዮጵያ መንግሥትና በኤርትራ በሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች መካከል በመጪው ጊዜ ሰፊ…