የሞዛምቢክ አሰልጣኝ ከጋዜጠኞች ጋር ተጋጩ ! በኢትዮጵያ ሽንፈት የገጠማቸው ሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቺኩንሆ ኮንዴ ከጋዜጠኞች ጋር ተጋጭተዋል። አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ከጋዜጠኞች ጋር ወደ ፀብ መግባታቸው ተገልጿል። ፀቡ ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ ከጋዜጠኞች በቀረበ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን በኋላም ወደ አካላዊ ግጭት አምርቷል። አስተያየት ለመስጠት በቦታው የተገኘው የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጣልቃ ገብቶ ግጭቱን ማረጋጋ…