ግዛትህ የማይደፈር ፣ ዙፋንህ የማይናወጥ፣ አንድነትህ የማይለያይ ፣ ሦስትነትህ ረቂቅ ፣ መንግሥትህ ስጋት የማያውቀው ፣ ቃልህ የማይታበል፣ ፍርድህ የማይዘናበል ፣ ጥበብህ የማይመከር፣ ማስተዋልህ የማይመረመር ፣ ምክርህ የማይፈርስ ፣ ፍቅርህ የማይቀየም ፣ ቸርነትህ የማይሰለች ፣ ምህረትህ የማያባራ ፣ ጥበቃህ የማይዘናጋ፣ ትዕግሥትህ እልፍ ፣ እጅህ የማይነጥፍ፣ ትከሻህ የማይዝል ፣ ሥልጣንህ የማይገሠሥ፣ ኪዳንህ የማይቀለበስ በጽድቅ እየፈረድህ…