🛑በደስታ እና በሀዘን መሀል አንድ ድልድይ አለ ሰላም። ሰላም ከሁሉ ይልቃል የህይወት ሚዛን ነውና። ደስታም ሆነ ሐዘን ወጀብ ናቸው - በዓይነት የተለያዩ ህመሞች። ሰላም ከነዚህ ሁለቱ ኋላ የሚመጣ ስክነት ነው። ሌላ ወጀብ እስኪመጣ የሚሰማን ዘላለማዊነት። በፊዚክስ ውስጥ የሚዛናዊነት (የEquilibrium) ጽንሰ ሀሳብ ማዕከላዊ ነው። አንድ ስርዓት በውጫዊ ኃይሎች ቢገፋም እንኳ ወደ መጀመሪያው ሁኔታው ወይም ወደ አዲስ የተረጋጋ ሁኔታ…